[go: up one dir, main page]
More Web Proxy on the site http://driver.im/Jump to content

ለሴ ፈር

ከውክፔዲያ

ለሴ ፈር (ፈረንሳይኛ laissez-faire «ያድርጉ» ወይም ቃል በቃል «ለማድረግ ፍቀዱ») ማለት ባለሥልጣናት በግለሠቦች መገበያየት ጥልቅ ሳይገቡ ቀርተው (ግፍ ወይም ሥርቆት ከመከልከል በቀር) የሚታገሡበት የምጣኔ ሀብት ዘዴ ነው።

በፈረንሳይኛ ዘይቤው «ለሴ ፈር» ከ1671 ዓም ጀምሮ እንዲታወቅ ይታመናል። ፍልስፍናው ከፈረንሳይ ይልቅ በታላቁ ብሪታን እንዲሁም በአውሮፓና በአሜሪካ ውስጥ ዘመናዊ ሆነ። በጥንቱ ቻይና ደግሞ ተመሳሳይ የአገዛዝ ፍልስፍና «ዉ ወይ» («ያለመሥራት») ይታወቅ ነበር። በለሴ ፈር ምክንያት የአውሮፓና የአሜሪካ ምጣኔ ሀብትና ንግድ ድርጅቶች ሊያብቡ እንደ ቻሉ፣ በፋብሪካ አብዮት በኩል ኑሮ ዘዴ እንዲለወጥና እንዲቀለል፣ አዳዲስ መጓጓዣና መገናኛ ፈጠራዎች እንዲገኙ ያስቻለው ሁሉ ይታመናል።

የፈጠራዎች ታሪክ ስንመለከት፣ ከ200 ዓክልበ. እስከ 1200 ዓም ያህል አብዛኞቹ አዳዲስ ፈጠራዎች የተደረጁ ከቻይና ነበረ፤ ወይም እስከ ሞንጎሎች ግዛት ድረስ። እንዲሁም ከ1500 እስከ 1940 ዓም ያሕል አብዛኞቹ አዳዲስ ፈጠራዎች የተደረጁ በምዕራባውያን አለም ነበረ።

በተቀራኒ በጀርመን ፈላስፋ ካርል ማርክስ ፍልስፍና ዘንድ ማንም ሕዝብ እንዳይበልጽጉ መቆጣጠር የመንግሥት ኃላፊነት ነው፣ ስለዚህ «ለሴ ፈር» ከ«ካፒታሊዝም» ጽንሰ ሀሣብ ጋር ይዘመዳል።